በጋምቤላ ተጨማሪ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

በጋምቤላ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ተደብቆ የነበረ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነግሯል ::

የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ም/ሃላፊ አቶ ኦቶው ኦኮት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት በጋምቤላ ከተማ ልዩ ስሙ 01 ቀበሌ አካባቢ በከተማዋ በሚገኘው ዩኒቨርስቲ ጀርባ ላይ ተደብቆ የተገኘ የጦር መሳሪያ በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

በቁጥር 12 ይደርሳል የተባለውን ይህንን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ደብቀው የተገኙ ተጠርጣሪ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ማጣራት እየተካሄደባቸው እንደሆነ ሃላፊው ነግረውናል፡፡

መነሻውን ደቡብ ሱዳን አድርጎ በህገ ወጥ መንገድ በከተማዋ ውስጥ የተገኘው ይህ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ለሽያጭና ለሌሎችም ዓላማ ሊውል እንደነበርም ተነግሯል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
የካቲት 22 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.