በአሜሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፍተኛ እዳዋ መመዝገቡ ተገለጸ፡፡

በአሜሪካ በፌደራል ደረጃ በጀት ነክ ጉዳችን የሚከታተለው በምህጻሩ CBO የአሜሪካ እዳ 28 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱን አስታውቋል፡፡

ይህም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ የተመዘገበው ከፍተኛው እዳዋ መሆኑ ነው ያስታወቀው፡፡

በአለም በገንዘብ የመጀመሪዋ አሜሪካ እዳዋ እንደዚህ እንዲጨምር ያበቃት ዋነኛው ምክንያትም ደግሞ የኮሮና ቫይረስ ይዞት በመጣው ጫና መሆኑን ነው CBO የገለጸው፡፡

በዚህም አሜሪካ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሲባል የህክምና ተቋማትን ለመገንባትና ክትባቶችን ለመምረት ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ አድርጋለች ብሏል፡፡

በተለይ ደግሞ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ስራ አልባ ለሆኑ ዜጎቿ ድጎማ የሚሆን ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ አድርጋለች ሲል አስታውቋል፡፡

በዚህም የአሜሪካ ጠቅላላ ኢኮኖሚ መቀነስ እያሰየ ሲሆን ይህም አሁን ያላትን በአለም በኢኮኖሚ የበላይነቷን አስጠብቃ ለመቆየትና ከቻይና ጋር ለምታደርገው እሽቅድድም ፈታኝ ሊሆን ይችላል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቦታል፡፡

በጅብሪል መሀመድ
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *