አሜሪካ ጥቅሟን ለማስከበር እንደምትሰራው ሁሉ ኢትዮጵያም ጥቅሟን ማስጠበቋን እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀው አሜሪካ የእራሷን ጥቅም ለማስጠበቅ እንደምትሰራው ሁሉ ኢትዮጵያንም ሉአላዊነቷን እና ጥቅሟን ለማስጠበቅ ትሰራለች ብሏል።

የሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ አምባሳደር ዲናሙፍቲ፣ አሜሪካ በቅርቡ በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ ያወጣችው መግለጫ ስህተት ነው ብለዋል ።

በተለይም ዋሺንግተን የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ከትግራይ ክልል ይውጣ ማለቷ ትክክል እንዳልሆነና የኢትዮጵያን ሉአላዊት የሚጋፍ እንደሆነም ተነስቷል።

ኢትዮጵያ የእራሷን የፀጥታ ሀይሎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል የማሰማራት መብት እያላት ይህ መባሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል አምባሳደሩ ።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ሆነ ከሌሎች አገራት የምትሰራው ብሔራዊ ጥቅሟን በአሰጠበቀ መልኩ ብቻ እንደሆነም አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው አብራርተዋል።

በአባቱ መረቀ
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *