ኢትዮጵያ ላለፉት 16 አመታት ስትጠቀምበት የነበረውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በአዲስ መተካቷን አስታወቀች።

የጤና ሚኒስቴር የቀጣይ 15አመት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ ፍኖተ ካርታን ይፋ አድርጓል ።

አዲሱ የኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፍኖተ ካርታም የጤና ተደራሽነትን ለማሳደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውም ታምኖበታል።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ለቀጣይ 15አመት እንዲያገለግል ይፋ የተደረገው ፍኖተ ካርታ፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ያገናዘበና ቴክኖሎጅን ማዕከል አድርጎ የሚሰራ ነው ብለዋል።

አሁን ላይ የበሽታዎች ባህሪ መለዋወጥ እያደገ በመምጣቱ የኤክስቴንሽን ፕሮግራምን በቴክኖሎጂ መደገፍ እንደሚያስፈልግ ዶክተር ሊያ አንስተዋል ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው የኤክስቴንሽን ፕሮግራም የማህበረሰብ ጤና አገልግሎትን ከማሳደጉ ባለፈ ለአገራዊ የህበረተሰብ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል የልማት አርበኛ ነው ብለዋል ።

ዘርፉ ለአገራዊ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ያነሱት አቶ ደመቀ፣የኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲደግፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።

የበፊቱን መመሪያ መቀየር ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያትም፣ ዘርፋን በተደረጃ መንገድ ለመምራት እንዲያስችልና የወቅቱን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ያገነዘበ በመሆኑ እንደሆነም ታውቋል።

በኢትዮጵያ የአለም የጤና ድርጅት ተወካይ ዶክተር ቦርማ ሀማ ሳምቦ ፣የኤክስቴንሽን ፕሮግራምን በመላው የአገሪቱ የገጠር ክፍል መዳረስ አለበት ፣ለዚህ ደግሞ የአለም የጤና ድርጅት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል ።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 39ሺህ 8መቶ78 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሚገኙ ሲሆን ይህም አንድ በለሙያ 5መቶ አባወራዎችን እንደሚያዳርስ ታውቋል።

አዲስ ይፋ የተደረገው የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ ከ2013 እስከ 2027 ድረስ ለቀጣዮቹ 15 አመታት የሚያገለግል ይሆናል ።

በአባቱ መረቀ
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *