ኢዜማ እጩ ተወዳዳሪዬ ከኮቪድ ነጻ ማስረጃ ካላመጣህ አንመዘግብህም ተብሏል አለ።

6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማድረግ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ በተሰጣቸው የጊዜ ሰሌዳ የእጩ ምዝገባ እያካሄዱ መሆኑ ይታወቃል።

እስካሁን 15 ፓርቲዎች እጩ ማስመዝገባቸውን የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ ከፓርቲዎች ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ተናግረዋል።

በዚህ የምዝገባ ወቅትም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዬ ከኮቪድ ነጻ ማስረጃ ይዘህ ካልመጣህ አንመዘግብም መባሉን አስታውቋል።

የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ግራር ጃርሶ ወረዳ እጩ ተወዳዳሪያቸው የኮሮና ነጻ ማስረጃ ያምጣ ስለመባሉ አረጋግጠውልናል።

ዛሬ ምርጫ ቦርድ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ውይይት በርካታ ፓርቲዎች የቅስቀሳ ሂደት ላይ ያጋጠማቸውን ችግር ተናግረዋል።

የእናት ፓርቲ የሀዋሳ ከተማ እጩ ተወዳዳሪ መንገድ ላይ ማስፈራሪያ እየደረሰባት ራሷን ማግለሏን ፓርቲው አስታውቋል።

በመቅደላዊት ደረጀ
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *