የህዳሴው ግድብ ሶስትዮሽ ድርድር በቅርቡ ይጀመራል የሚል እምነት እንዳላት ኢትዮጵያ አስታወቀች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት የሚካሄደው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት በቅርቡ ይጀመራል ብሏል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል ።

አምባሳደር ዲና በዚህ ወቅት እንዳሉት የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ዲሞክራቲክ ኮንጎ ድርድሩን ለማስጀመር ከሶስቱ አገራት ጋር እተነጋገረች ነው ብለዋል።

ዲሞክራቲክ ኮንጎ አደራዳሪዎችን ወደ ካይሮ፣ካርቱምና አዲስአበባ በመላክ በድርድሩ ዙሪያ እንደመከሩም አምባሳደር ዲና አንስተዋል።

ደቡብ አፍሪካ ለህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ላደረገችው ጥረት ኢትዮጵያ ምስጋና ታቀርባለች፣ አዲሷ የህብረቱ ሊቀመንበር ዲሞክራቲክ ኮንግ ድርድሩን እንምታሳካ ተስፋ እንዳላትም ቃል አቀባዩ ተናግረዋል ።

በአባቱ መረቀ
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.