ቦርዱ በምርጫ ጉዳዮች ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በአዲስ አበባ እየመከረ ነው።
ቦርዱ በዚህ ጊዜ እንዳለው እስካሁን ድረስ 15 ፓርቲዎች በ673 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ምዝገባቸውን አካሂደዋል ብሏል።
እነዚህ ፓርቲዎች ከ2ሺ በላይ እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋልም ተብሏል።
እስካሁን በተካሄደው የዕጩዎች ምዝገባ ሂደት ኢዜማ ፣ብልጽግና፣ አብን፣ ኢሶዴፓ
፣ ህብር ለኢትዮጵያ፣ሲዴፓ እና የአፋር ህዝብ ፓርቲ ችግር ደርሶብናል ብለው ነበር ብሏል ቦርዱ።
ከጸጥታ እና ደህንነት ጋር በተያያዘ መተከል ዞን ፓርቲዎች ችግር እንደገጠማቸው አሰምተዋል።
የምርጫ ቦርድ ቢሮዎችን ያለማወቅ በእጩዎች በኩል የተነሱ ጥያቄዎች ናቸው።
በሀረር ክልል የአብን እጩ የነረበ ሰው ታስሮ ከፕሬዝደንቱ ጋር በቶሎ በማውራት ተፈትቶ ምዝገባውን አድርጓልም ተብሏል።
በመቅደላዊት ደረጀ
የካቲት 24 ቀን 2013 ዓ.ም











