ሊያና ዲጂታል ሄልዝኬር ሶሉዩሽን የቴሌ ሄልዝ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ገለፀ።

የሊያና ሄልዝኬር ሶሉዩሽን ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በበይነ መረብ አማካኝነት በርቀት የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን በሙሉ ማጠናቀቁን ገልጿል።

የድርጅቱ ባልደረባ የሆኑት ዶክተር ግርማ አባቢ እንደገለፁት አገልግሎቱን መጠቀም የሚያስችሉ ”7755” የመደወያ ቁጥር፣ ዳታ ቤዝና መተግበሪያዎች ተዘጋጅተዋል ብለዋል።

አካሚዎችና ታካሚዎች በየትኛውም ቦታ ሆነው ኢንተርኔትንና መተግበሪያዎችን በመጠቀም፣ የጤና ነክ መረጃዎችን በመለዋወጥ የሚደረግ እንደሆነም አስረድተዋል።
መረጃዎቹ በሞባይል አማካኝነት በድምፅ፣ በተንቀሳቃሽ ምስልና በጽሁፍ መልክ ሊቀመጡ እንደሚችሉ ነዉ የተናገሩት።

አገልግሎቱ በሀገራችን ሩቅ ቦታ ለሚገኙና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎትን ማግኘት ለማይችሉ ሰዎች በቀላሉ አገልግሎቱን ማግኘት ያስችላቸዋል ብለዋል።

በተለይም የኮቪድ_19 ታካሚዎች ባሉበት ሆነው ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር ክትትል ለማድረግ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነው ያሉት።

ይህንን ቴክኖሎጂ በመጠቀም አሁን ባለው የቴክኖሎጂ እድገት 70 ከመቶ የሚሆኑ በሽታዎችን ማከም እንደሚቻል አስታውቀዋል።

በጅብሪል ሙሃመድ
የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.