በመቀሌ ከተማ ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ማሳየቱ ተነገረ፡፡

ከተማዋ እለት ተእለት ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች መሆኗን የመቀሌ ከተማ ጊዜያዊ ከንቲባ የሆኑት አቶ አታክልቲ ሃ/ስላሴ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ ጥሩ መሻሻሎች እየታዩ ነው ያሉን አቶ አታክልቲ ከተማዋን በመረጋጋቱ ሂደት ላይ የነበሩ ዋና ዋና ስጋቶችም እለት ተእለት እየተቀረፈ እንደሆነ ነግረውናል፡፡

ከተማዋ እንዳትረጋጋና ሰላም እንዳትሆን ያልተገባ ወሬን የሚነዙ አካላት አሁንም ቢሆን በጊዜያዊ አስተዳዳሩ እንቅስቃሴ ላይ ትልቅ ዋጋ እያስከፈሉ መሆኑን ያነሱልን አቶ አታክልቲ ህብረተሰቡ ባልተገባ መልኩ ከሚነዙ አሉባልታዎች እራሱን በመጠበቅ የሚሰማውን አጣርቶ ከምንም በላይ የሚያየውን ሰላማዊ እንቅስቃሴ መደገፍ እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎች እየተደረጉ መሆኑንም ያነሱልን ከንቲባው እስካሁን ወደ 3 መቶ ሺ ለሚሆኑ ዜጎች እርዳታ እንዲያገኙ መደረጉንም ነግረውናል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ተቋማትም ወደ ስራ እየተመለሱ እንደሆነና በቀጣይ ትምህርት ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስጀመር እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች መኖራቸውንና በተመሳሳይ ፍርድ ቤቶችን በከተማዋ በሚገኙ ሁሉም ክ/ከተሞች ላይ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛል ብለውናል፡፡

ነገር ግን በ አብዛኛው በጦርነቱ የወደሙ ተቋማትን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.