በማያንማር ተቃውሞ የ38 ዜጎች ተገደሉ፡፡

በትላንትላው እለት ብቻ የሃገሪቱ ዜጎች ወታደራዊውን ጊዜያዊ መንግስት በወጡ 38 ሰዎች ላይ እርምጃ መውሰዱ ተነግሯል፡፡

የተባበሩት መንግስታት እንዳለው በማይናማር ከአንድ ወር በፊት በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስቱ ላይ የሚካሄደው ተቃውሞ ሲቀጥል በትናንትናው እለት ግን በተቃዋሚዎች ላይ የደረሰው ግድያ “እጅግ ደም አፍሳሽ ቀን” ነው ብሎታል፡፡

በማይናማር የተባበሩት መንግስታት ልዑክ ክርስቲን ሽራነር በተቃውሞ ሳቢያ በሀገሪቱ አስደንጋጭ ቪዲዮዎች እየወጡ እንዳሉም ተናግረዋል ፡፡

የፀጥታ ኃይሎች በተቃዋሚዎች ላይ የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን የዓይን እማኞች ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወታደራዊ ኃይሉ የካቲት 1 ቀን ስልጣኑን ከተቆጣጠረበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ተቃውሞ እና ህዝባዊ የእምቢተኝነት ድርጊቶች በመላው ማያንማር ታየቱ ቀጥሏል፡፡

ሰልፈኞቹ ወታደራዊ አገዛዙ እንዲነሳ እና በመፈንቅለ መንግስቱ የተያዙት ኦንግ ሳን ሱቺ ን ጨምሮ በሀገሪቱ የተመረጡ የመንግስት መሪዎች እንዲለቀቁም ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡

በየውልሰው ገዝሙ
የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.