በአለም ትልቁ የምግብ እና መጠጥ ኩባንያ ኔስሌ በኢትዮጵያ ስራ ጀመረ፡፡

መቀመጫውን በስዊስ ያደረገውና እ.ኤ.አ በ1867 የፋርማሲ ባለሙያ በነበረው ሄንሪ ኔስሌ የተመሰረተው ጉባንያው፤ ለህጻናት እድገት አስፈላጊ የሆነውንና በወተት ተዋጽኦ የበለጸገውን ሴሬላክ የተባለውን ምግብ አምራች ድርጅት መሆኑ ይታወሳል፡፡

ኩባንያው ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መረጃ፤ ኔስሌ ሴሬላክ ከወተት ጋር ተቀላቅሎ የተሰራ የሕጻናት ምግብ በመሆኑ በተለይም እድሜያቸው ከ6 ወራት በላይ ለሆኑ ህጻናት የሚሆን ነው ብሏል፡፡

ምርቱ ከወተት፤ ከስንዴ፣ ከሙዝ ጋር ተቀምሞ የተዘጀ ሲሆን፣ ይህም በቫይታሚን ኤ እና ሲ፣ አይረን፣ አዮዲን፣ ኦሜጋ 3 እና ቫይታሚን ቢ የበለጸገ መሆኑ ተነግሯል፡፡

እነዚህ የቫይታሚን አይነቶች ደግሞ በሳይንሳዊ ጥናቶች መሰረት ለሕፃናት የአእምሮ እና የግንዛቤ እድገት ለማምጣት አስፈላጊ መሆናቸው ተረጋግጧል ብሏል ኩባንያዉ፡፡

በተጨማሪም የዳበሩ የሕፃናት ተጨማሪ ምግቦች የአይረን እጥረት እና የደም ማነስ ጉዳትን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ እንደሆነም አስረድቷል፡፡

እንዲሁም ደካማ የአመጋገብ ልማድን በማሻሻል፣ በምግብ እጥረት የሚያጋጥሙ ጉዳቶችንና ሞትን ይቀንሳል ብሏል፡፡

ኩባንያው በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴርና በዘርፉ ባለሙያዎች ምግቡ ለህጻናት እድገት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዘ መሆኑን ማረጋገጫ እንደተሰጠው ገልጿል፡፡

በዚህም ምርቱን በመላው ኢትዮጵያ ባሉ በተለያዩ ሱፐር ማርኬቶች፤ በመድሃኒት ቤቶች፣ በሆስፒታሎችና ጅምላ አከፋፋዮች ማሰራጨቱን አስታውቋል፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *