ጠንካራ ባልሆነ ተቋም እና በዕውቀት ማነስ ምክንያት እግረኞች ላይ የትራፊክ አደጋ እንደሚደርስ ተነገረ፡፡

በኢትዮጲያ ካለው የአስፓልት መጠን ዝቅተኛ የሆነ የእግረኛ መንገዶች ቢኖሩም ከነርሱ ውስጥም አገልግሎት የማይሰጡም እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡

በዛሬው እለት እግረኞች ለምን የእግረኛን መንገድ መጠቀም አቃታቸው በሚለው ላይ በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አዘጋጅንት የውይይት መድረክ በተዘጋጀበት ወቅት ነው ይህ የተገለፀው፡፡

በኢትዮጲያ ከአጠቃላይ የአስፓልት መንገዶች 35 በመቶው ብቻ የእግረኛ መንገድ መኖሩን እና ከዛም ውስጥ በተለያየ ሁኔታ ከጥቅም ውጪ የሆኑ እና አገልግሎት የማይሰጡ የእግርኛ መንገዶችም እንዳሉ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ላይ ጥናት ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እና በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር በለጠ እጅጉን አናግረን ጠንካራ የሆነ የሚመራ እና የሚያስተዳድር ተቋም ባለመኖሩ ምክንያት፣ እግረኞች ለትራፊክ አደጋ እየተጋለጡ ነው ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ጠንካራ የሆነ የሚመራ እና የሚያስተዳድር ተቋም ካለመኖሩም ባሻገር፣ የእግረኞች የዕውቀት ማነስ፣አስተዋጽኦ የእግረኛ መንገድ ያለመኖር ፣ የእግረኛ መንገድ መጥበብ ፣ ለሌላ ጥቅም እየዋለ በመሆኑ እና የደምብ ማስከበር ጉድለት ለችግሩ መባባስ ማድረጋቸዉን ዶ/ር በለጠ እጅጉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በረድኤት ገበየሁ
የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *