ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ክትባቷን የፊታችን አሁድ ወደ አገር ውስጥ ልታስገባ መሆኑን አስታወቀች።

የጤና ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የኮቪድ-19 ለመከላከል የሚውል የመጀመሪያው ዙር ክትባት ወደ ሀገር ውስጥ የፊታችን እሁድ በ28/06/213 ዓ.ም ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል።

በክትባቱ ርክክብ ላይም የመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች በተገኙበት እንደሚካሄድ ሚንስቴሩ ገልጿል።

ይሁንና ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የክትባት መጠን አልተገለጸም።

በየውልሰው ገዝሙ
የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *