የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በ6 ወራት ውስጥ ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገለፀ።

የድርጁቱ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የ2013 ዓም የመጀመያ 6 ወራት አፈጻጸምን ባቃረቡበት ወቅት እንዳሉት ለመሰብሰብ ከታሰበው ገቢ 90 በመቶውን ማሳካት ችለናል ብለዋል።

ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር የ10 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል።

ገቢው የተሰበሰበውም ድርጅቱ በሚሰጣቸው ዋና ዋና አገልግሎቶቹ ማለትም በፖስታ ደብዳቤ፣ በፈጣን መልዕክት፣ ፖስት ቢዝና በቤት ለቤት እንዲሁም በሌሎች ስራዎች መሆናቸውን ነው የገለፁት።

ድርጅቱ ከኢትዮጵያ መልእክቶችን በዓለም ወደ 90 ሀገራት ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ሃላፊዋ፣ አሁንም አዳዲስ አገልግሎቶችን በመጀመር ለደንበኞቹ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እንደሚሰራም አስታውቀዋል።

በጅብሪል ሙሃመድ
የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *