ትራምፕ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶብኛል አሉ፡፡

የቀድሞው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሪፐብሊካን አባላት ስማቸውን የማጥፋት ዘመቻ እንደከፈቱባቸዉ ተናግረዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ የበላይነትን አጥብቀው የሚሰብኩና በንግግራቸው ግድ የለሽነት የሚታይባቸው ፕሬዝዳንት ናቸዉ በሚል ሲተቹ ነበር፡፡

በተለይም በስልጣን ማጠናቀቂያቸዉ ላይ ደጋፊዎቻቸውን በማስተባበር በካፒቶል ህንፃ ላይ አመፅ እንዲነሳ አድርገዋል በሚል በክስ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።

በአመፁም የ5 ሰዎች ህይወት እንዲጠፋና በሪፐብሊካኑ መካከል መከፋፈል እንዲኖር አድርገዋል በሚል ስማቸዉ በአሉታዊ መልኩ ይነሳል፡፡

ይህን ተከትሎ ትራምፕ አንዳንድ የሪፐብሊካን አባላት ስሜን ለማጥፋት ሲሉ የገንዘብ እርዳታ ያደርጋሉ፤ ከዚህ ድርጊታቸዉ ሊታቀቡ ይገባል ሲሉ ተሰምተዋል።

በአማካሪያቸውና ጠበቆቻቸው አማካኝነትም ቅሬታቸውን ለሪፐብሊካኑ ማቅረባቸው ታዉቋል፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *