የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የሂሳብ ሙያን የሚደግፍ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የሂሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች ማህበር በኢትዮጵያ የዘርፉ ተቆጣጣሪ አካል ከሆነው ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ውስጥ የሂሳብ ሙያ ልማትን የሚደግፍ ፕሮጀክት ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል ተብሏል።

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፤ ፕሮጀክቱ በፋይናንስ ሚኒስቴር በሚተዳደር ገንዘብ አማካኝነት በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል፡፡

የተመሰከረላቸው የሂሳብ እና ኦዲት ባለሙያዎች ማህበር እና የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ በመካከላቸው ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚረዳም ታዉቋል፡፡

ፕሮጀክቱ የሙያውን እና የበርካታ ባለድርሻ አካላትን ፍላጎቶች ለማሟላት የሚያስችል ጠንካራ ስትራቴጂ ያለው አግባብ የሆነ ብሔራዊ አካል እንዲቋቋም ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናልም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ሥራው ይበልጥ ጠንካራ የሆነ፣ ለጉዳዩ የሚመጥን እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟላ የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት እና ዓለም አቀፍ የደረጃ መስፈርቶችን በማክበር ላይ አተኩሮ እንደሚንቀሳቀስ ቦርዱ አመላክቷል፡፡

የማህበሩ የገበያ አጋርነት እና ዕውቅና ዳይሬክተር ስቴፈን ሺልድስ ፕሮጀከቱ፤ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ እንደሆነና የህዝቡን ጥቅም የሚያስጠበቅ ነዉ ብለዋል ።

የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ ዋና ዳይሬከትር ወ/ሮ ሂክመት አብደላ በበኩላቸው ፤በሂሳብ እና በኦዲት ባለሞያዎች እንዲሁም በሙያው ላይ ቁጥጥር በማድረግ የህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ አስፈላጊ የሆኑት ማስፈጸሚያዎች አሉት” ብለዋል።

በአባቱ መረቀ
የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *