ፍቅር እስከ መቃብር መጽሀፍ በአለም አቀፍ ቋንቋዎች ሊተረጎም ነው፡፡

በደራሲ ሐዲስ አለማየሁ የተጻፈው ፍቅር እስከመቃብር (ልብ-ወለድ በ1958 ዓ.ም) መጽሃፍ በሀገራችን በርካታ አንባቢያንን ያፈራ ተወዳጅ ድርሰት እንደሆነ ይገለጻል፡፡

መጽሃፉን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተደራሽ ለማድረግ በእንግሊዝኛና በዓረብኛ ልሳኖች ለማስተርጎም የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ተፈራ መላኩ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ ከሼክስፒር ድርሰቶች ውስጥ ሮሜዎና ጁሌት አለም አቀፍ እውቅናን ያተረፉት በዚሁ መንገድ ነው ብለዋል፡፡

ቢሆንም ግን ከፍቅር እሰከመቃብር ይዘት ጋር ሲነጻጸር በምንም አይገናኝም ነው ያሉት፡፡

ሮሜዎና ጁሌት ንጹህ ፍቅር ብቻ መሆናቸውን ያወሱት ፕሬዝዳንቱ በፍቅር እሰከ መቃብር ውስጥ ግን በፍቅር ውስጥ፤ የአንድን ሀገር ባህል፤ እምነትን፤ መንግስታዊ አወቃቀርንና ሌሎችን ጉዳዮች የያዘና በአጻጻፍ ጥበቡና የአገላለጽ ስልቶቹ የረቀቁ ናቸው ብለዋል፡፡

ነገር ግን እስካሁን ደረስ የታሪክና የሃሳብ ይዞታውን ያህል ድርሰቱ ዓለም አቀፍ እውቅናን አላገኘም ብለዋል፡፡

ስለሆነም በዩኒቨርሲቲያቸው የልህቀት ማእከል ውስጥ ኢትዮጵያውያን ድርሰቶችን ዓለምአቀፍ እቅውናን እንዲያገኙ ለማድረግ ወደፊት እንደሚሰራም ነግረውናል፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *