20 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው የሎተሪ እጣ የአሸናፊው ጊዜ ነገ ያበቃል፡፡

ጳጉሜ 2012 የወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ እስካሁን ድረስ አሸናፊው እንዳልታወቀ ተገልጾ ነበር፡፡

20 ሚሊየን ብር የሚያሸልመዉ የሎተሪ እጣው የአሸናፊ ጊዜው በነገው እለት እንደሚያበቃ ነው አስተዳደሩ ያስታወቀው፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ የ20 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው የሎተሪ አሸናፊ በነገው እለት ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡

የእጣ ቁጥሩ ከወጣ ስድስት ወራቶች ቢያስቆጥርም፣ እስካሁን ድረስ አሸናፊ ሆኖ የቀረበ እና ሽልማቱን የወሰደ ግለሰብ የለም ተብሏል፡፡

ጳጉሜ አምስት ቀን የወጣው የ20 ሚሊየን ብር አሸናፊ የእጣ ቁጥር 0216884 እንደነበረ ይታወቃል፡፡

አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮ ኤፍ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት የሎተሪው አሸናፊው ነገ መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም የሚያበቃ ይሆናል፡፡

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በአዲስ መልክ ለሁለት ተከታታይ ጊዜ የ20 ሚሊየን ብር እጣ አዘጋጅቶ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡

ለመጀመርያ ጊዜ ያቀረበው 20 ሚሊየን ብር የሚያሸልመው እጣ በጊዜው ለአሸናፊው ማስረከቡንም አስታውቋል፡፡

ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በተለያዩ ጊዜያቶች ከፍተኛ መጠን ያላቸው የሎተሪ አይነቶች አሸናፊያቸው ሳይታወቅ ተመላሽ መሆናቸውንም አስታዉሷል፡፡

ተመላሸ ከሆኑ የሎተሪ አይነቶች መካከል የጸሐይ ሪል እስቴት መኖርያ ቤት፣ የዘነበ ፍሬው መኖርያ ቤት እና ቤት መስርያ ቦታ ይገኙበታል፡፡

እስከ ነገ መጋቢት አንድ ቀን ድረስ የሎተሪ አሸናፊው የማይታወቅ ከሆነ ተመላሽ እንደሚሆንም ነዉ የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ያስታወቀዉ፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
የካቲት 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *