በትግራይ ክልል ለ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዜጎች ድጋፍ መድረጉ ተነገረ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በትግራይ ክልል በነበረው የህግ ማስከበር ሂደት ለተጎዱ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብሏል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ላይ ሲሆኑ ፣ ለ 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን የክልሉ ዜጎች የሰባዊ እርዳታ ድጋፍ ተደርጓል ነው ያሉት።

በኡሁ ወቅት በትግራይ ክልል እየተደረገ ባለው የሰባዊ እርዳታ 70 በመቶ የሚሆነው የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው ብለዋል።

ምዕራባውያንም ሆኑ ሌሎች የአለም አገራት በትግራይ ክልል ባለው ነገር ተቆርቋሪ ነን ቢሉም እያደረጉት ያለው ድጋፍ ግን አነስተኛ እንደሆነም አምባሳደሩ አንስተዋል።

የአለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶች በትግራይ ክልል የሰባዊ እርዳታ እያደረጉ ያሉት 30 በመቶ ብቻ እንደሆነም ታውቋል።

የአለም የምግብ ፕሮግራም ድርጅት ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን የሰባዊ እርዳታ ማድነቁንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል። መንግስት በክልሉ ተፈፅሟል ስለተባለው የሰባዊ ጥሰት ለመመርመርም ከጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ከሰባዊ መብት ኮሚሽን እና ከሌሎችም አካላት ጋር በመሆን ለመመርመር ዝግጁ መሆኑም በመግለጫዉ ተነስቷል።

በየመን በደረሰው የእስር ቤት ቃጠሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወታቸው ማለፉን የገለጹት የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በአደጋው ህይወታቸው ያለፈ ኢትዮጵያውያን ትክክለኛ ቁጥር እየተጣራ መሆኑን ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

በአባቱ መረቀ
የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *