በኢኳቶሪያል ጊኒ በደረሰው ፍንዳታ የሟች ቁጥር 98 ደርሷ፡፡

ከትላንት በስቲያ ዕሁድ በደረሱት ተከታታይ ፍንዳታዎች 615 ሰዎች መጎዳታቸው እና 299 ያህሉ ደግሞ በሆስፒታል ህክምና ላይ መሆናቸውን የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል፡፡

አደጋው የደረሰው በሀገሪቱ የንግድ ማዕከል ናት በምትባል ባታ ወደብ ላይ ነው፡፤
የፍንዳታው መነሻ ምክንያት እስካሁን ባይታወቅም ከወታደራዊ ካምፕ ሊነሳ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ፍንዳታው በአግባቡ ባልተቀመጠ ድማሚት አካባቢ እንዳለ ገልጸው በአቅራቢያው ያሉ አርሶ አደሮችም ከጥንቃቄ ጉድለት ባቀጣጠሉት ገለባ ምክንያት አደጋው መድረሱን ያነሳሉ፡፡

አሁንም የነፍስ አድን ዘመቻው እንደቀጠለ ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ዘገባው እንደሚለው ምንአልባትም የሟቾች ቁጥር በግምት 31 ይሆናል ቢባልም አሁን ባለው ሁኔታ ግን በሦስት እጥፍ ሊበልጥ ይችላል፡፡

ከዚህ አደጋ ሶስት ሕፃናት በሕይወት ተገኝተው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

በከተማው ውስጥ ያሉ ሁሉም ሕንፃዎች እና ቤቶች ማለት ይቻላል “ከፍተኛ ጉዳት” ደርሶባቸዋል ሲሉ ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉማ ተናግረዋል ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.