ትላንት ለሽምግልና በተቀመጡ የጉጂ እና የአማሮ ተወካዮች ላይ በተከፈተባቸው ድንገተኛ ተኩስ የስድስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

ትላንት በጉጂ ወረዳና በአማሮ ልዩ ወረዳ መካከል በህብረተሱ መካከል የተከሰተውን ዕለታዊ ግጭት እና አለመግባባት በእርቀ ሰላም ለመፍታት በተቀመጡ የሀገር ሽማግሌዎች ፤የወረዳው አመራሮች እንዲሁም የጸጥታ አካላት ላይ የኦነግ ሸኔ አባላት ናቸው የተባሉ በሰነዘሩት ድንገተኛ ጥቃት ስድስት ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ በርካቱች መቆሰላቸውን የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ለኢትዩ ኤፍ ኤም ገልፀዋል፡፡

የቢሮው ሀላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ከኢትዮ ኤፍ ኤም የማለዳ ዜና ጋር በስልክ በነበራቸው ቁይታ እንደተናገሩት ጥቃቱ ከመዘናጋት የደረሰ ነው፡፡

አቶ አለማየሁ እንደሚሉት ይህ ቡድን በተለያየ ጊዜያት አሳሳች ሰአት ላይ እየጠበቀ ጥቃት ይሰነዝር ነበር ፡፡

ይሁን እንጂ ላለፉት አምስት ወራት የኦነግ ሸኔ አባላት ይኖሩበታል በሚባሉ አካባቢዎች የተጠናከረ የጸጥታ ማስከበር ዘመቻ ሲደረግ መቆየቱን እና ይደርስ የነበረው ጥቃትም መቀነሱን የሚናገሩት ሀላፊው፡፡

አሁን የደረሰው ጥቃትም ጠፍቷል የለም ከሚል መዘነጋት አስፈላጊ ጥንቃቄ ካለማድረግ የተከሰተ ነው ይላሉ፡፡

በዚህ አደጋ በጣም አሳዛኛ በሆነ ሁኔታ ክቡር የሆነው የሰው ህይወት ፤ ክቡር ከሆነው ሽምግልና ስፍራ አልፏል ብለውናል አቶ አለማየሁ፡፡

የክልሉ መንግስት በቀጣይ ምርጫ መሆኑን ተከትሎና ቡድኑ ተመሳሳይ ጥቃት ፈፅሞ ከማዘናችን በፊት ከአጎራባቹ ኦሮሚያ ክልል ጋር የተጠናከረ ዘመቻ ለማድረግ ምክክር ላይ ነን ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *