የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሁለት የቢራ ፋብሪካዎች ላይ የማሸግ እርምጃ መዉሰዱን አስታወቀ፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እንዳለዉ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ሁለት የቢራ ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተለያዩ የድጋፍ ማዕቀፎችን ዘርግቶ በመንቀሳቀስ ላይ ቢገኝም አንዳንድ የማኑፍክቸሪንግ ተቋማት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ ነዉ ተብሏል፡፡

የጥራት የንግድ አሰራርና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ እሸቴ አስፋው፤ ይህንንም ተከትሎ በተደረገ ክትትል ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ አድርገው በተገኙ ሁለት የቢራ ፋብሪካዎች ላይ የማሸግ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊት የቢዝነስ ፕላን ማዘጋጀት ሲኖርባቸው የራሳቸውን ትርፍ ለማስፋት ሲሉ እንደፈለጉ የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርጉም አንስተዋል፡፡

ሁሉም የማምረቻ ተቋማት እንደዚህ ያለ ተግባር ከመፈጸም መቆጠብ እንዳለባቸውና በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰል ስርዓት አልበኝነትን ለመቆጣጠር የቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚኒስቴር ዴኤታዉ አሳስበዋል፡፡
በአባቱ መረቀ
የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.