በስራ ላይ ያለዉ የኢትዮጵያ ሳይንስ፤ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ፖሊሲ ለስራ ፈጠራ ትኩረት የነፈገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሚንስቴሩ ይህን ፖሊሲ በመሻሻል ላይ የሚገኝ ሲሆን የተሻሻለዉ ፖሊሲ ስራ ፈጠራን ማእከል ማድረግ እንደሚገባው ተጠቁሟል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳ ረቂቅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ግብዓት እየሰበሰበ ይገኛል፡፡

ስራ ላይ ያለው ፖሊሲ ስራ ፈጠራን ማዕከል ያላደረገ፣ የግሉ ዘርፍ በቴክኖሎጂ የመሪነት ሚና እንዲኖረው ያላስቻለና የቴክኖሎጂ ልማት ከኢኖቬሽን ጋር በሚፈለገው መልኩ ያላስተሳሰረ በመሆኑ ነው ክለሳ ማድረግ የተፈለገው ተብሏል፡፡

የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አህመዲን መሀመድ አዲሱ ፖሊሲ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንን በመጠቀም የኢኮኖሚው ማሻሻያ ግብ የሆኑትን የስራ እድል ፈጠራ ማሳካት፣ የውጭ ገቢን ማሳደግና ሀገራዊ ብልፅግናን ማምጣትን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

ረቂቅ ሰነዱ የግሉ ዘርፍ በቴክኖሎጂ የመሪነት ሚና እንዲጫወት የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመዋል።

የፖሊሲ ክለሳው የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፖሊሲ ክለሳ ጥናት፣ የአገር በቀል የኢኮኖሚ አጀንዳ፣ የ10 አመት አገራዊ እና የዘርፍ ዕቅድ፣ ዘላቂ የልማት ግቦች 2030፣ የአፍሪካ የሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስትራቴጂ 2024 እንዲሁም አለም አቀፋዊ ልምዶችን መነሻ አድርጎ የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልቷል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ፖሊሲው የሚፈለገው ግብዓት ከተሰበሰበ በኋላ በሚመለከተው አካል ፀድቆ ስራ ላይ እንዲውል ይደረጋል ሲል አስታውቋል፡፡

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *