በአዲስ አበባ በስድት ወራት ውስጥ ከ 5 ሺህ በላይ ወንጀሎች ተፈጽመዋል ተባለ፡፡

በመዲናዋ ከሀምሌ 1 ቀን 2012 አንስቶ እስከ ታህሳስ 2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ 5ሺህ 657 ወንጀሎች መፈጸማቸዉ ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በመዲናዋ ከተፈጸሙ ወንጀሎች መካከል ከ 3ሺህ በላይ የሚሆኑት እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተናግረዋል፡፡

ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ የተያዙትም በህብረተሰቡ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ጥረት መሆኑን ጨምረዉ ተናግረዋል፡፡

በዚህም በከተማዋ እጅግ ከባድ ወንጀሎች በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሳቸውን ነው ኮማንደር ፋሲካው የተናገሩት፡፡

በመዲናዋ ለህዝቡ ስጋት የነበሩ ወንጀሎች በ17 መቶ መቀነሳቸዉንም ነዉ ኮማንደር ፋሲካዉ የገለጹት፡፡

ይህ ማለት በቁጥር ሲገለጽ 1ሺህ 200 ወንጀሎች በመዲናዋ ቀንሰዋል ብለዋል፡፡
ከባድ ወንጀሎች የሚባሉት እስከ ጦር መሳርያ ዘረፋ ድረስ የሚደርሱ 11 ከባድ ወንጀሎች ናቸው ብለዋል፡፡

በመዲናዋ በተደጋጋሚ ይስተዋሉ የነበሩት የመኪና ስርቆት፣ በመኪና ወስጥ የንብረት ዘረፋ እንዲሁም የጦር መሳርያ ዘረፋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሳቸውን ኮማንደር ፋሲካው ነግረዉናል፡፡

በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.