ከኢህዴን መስራቾች አንዱ የሆኑት ብ/ጄ አከለ አሳዬ አረፉ፡፡

ብ/ጄ አከለ አሳዬ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በ1961 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
በ17 ዓመታቸዉ የደርግ ስርዓትን ለመገርሰስ በአካባቢዉ ሲንቀሳቀስ የነበረዉን የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢህዴን)ን ተቀላቀሉ፡፡

ከዚያም ከ1978 እስከ 1979 በተራ ተዋጊነት፣ከ1979 እስከ 1980 በ8ኛ ሻምበል ምክትል ቲም መሪነት እንዲሁም በአዋሽ ክ/ጦር ሬንጅመንት ኮሚሳር በመሆን ከ1981 እስከ 1984 ዓ.ም አገልግለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ የዓለም አቀፍ ስምሪቶች ተሳትፎ አድርገዋል፡፡

በጡረታ እስተገለሉበት 2004 ዓ.ም ድረስም ለ26 ዓመታት በተለያዩ ወታደራዊ የሃላፊነት ደረጃዎች ሀገርና ህዝባቸዉን ማገልገላቸዉን የህይወት ታሪካቸዉ ያስረዳል፡፡

ብ/ጄ አከለ አሳዬ “ያልተንበረከኩት”ና “በድልና በመስዋትነት የደመቀዉ የኢህዴን ሰራዊት ታሪክ” የሚሉ መጻህፍትን ለንባብ አብቅተዋል፡፡

ብ/ጄ አከለ አሳዬ ባደረባቸዉ ህመም በጦር ሃይሎችና ጳዉሎስ ሆስፒታል ሲረዱ ቆይተዉ በትናንትናዉ እለት የካቲት 30/2013 ዓ.ም በ52 ዓመታቸዉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ብ/ጄ አከለ አሳዬ ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡
ስርዓተ ቀብራቸዉም በዛሬዉ እለት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *