በላይአብ ግሩፕ ከአፍሪካ የመድሀኒት አከፋፋይ ከሆኑት ከኤም ፋርም እና ከሀልተን ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት አድርጓል፡፡
ወደ መድሀኒት ዘርፉ የተቀላቀለው በላይአብ ፋርማሲስቲካልስ፣ በኢትዮጵያ የመድሀኒት እጥረትን ለመቅረፍ የሚያስችል ስምምነት ማድረጉን ነው ያስታወቀው፡፡
ስምምነቱ በዋናነት በመድሀኒት አቅርቦት ላይ ትኩረት አድረገው የሚሰሩ ሲሆን፣ የመድሀኒት ጥራት ለማረጋጋጥ እና እነዚህ ሁለት ተቋማት በመድኒት አቅርቦቱ የሚጠቀሟቸውን ሰንሰለቶች ለመጠቀም የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
የበላይአብ ፋርማሲስቲካልስ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ሮቤል ምናሴ እንደተናገሩት፣ በላይ አብ ፋርማሲ ዘንድሮ በአዲስ አበባ ሁለት አዲስ ፋርማሲ ቤቶችን ለመክፈት ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
ማናጀሩ አክለው በሚቀጥለው አመት ተጨማሪ 30 ፋርማሲ ቤቶችን ለመክፈት አስነበናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኤም ፋርም በአፍሪካ ግዙፉ የመድሀኒት አቅራቢ ድርጅት ሲሆን በአፍሪካ ጋና መቀመጫውን አድርጎ ቴክኖሎጂን ከጤናው ዘርፍ ጋር በማቀናጀት እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
በአሁኑ ሰአት ደግሞ በአምስት ሀገራት በመድሀኒት አቅርቦት ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡
ሀልተን የተሰኘው ፋርማሲ ደግሞ በመላው አፍሪካ ከ300 በላይ ፋርማሲዎችን ከፍቶ በየወሩ እስከ 100ሺህ ለሚደርሱ በሽተኞች ታማሚዎች እያቀረበ የሚገኝ ተቋም መሆኑ ተገልጿል፡፡
እነዚህ ተቋማት ባደረጉት የጋራ ስምምነት በየፋርማሲ ቤቶቹ የላብራቶሪ ምርመራ እንደሚያደርጉም ነው ያስታወቁት፡፡
ሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 02 ቀን 2013 ዓ.ም











