አሜሪካ የሞዛምቢክ እና የዲሞክራቲክ ኮንጎ አማጽያንን በአሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ አስፍራለች፡፡

አሜሪካ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በሞዛምቢክ ያሉ አማጺያን ቡድኖችን አሸባሪ ድርጅቶች ስትል ሰይማለች፡፡

በሽብርተኝነት መዝገብ የሰፈሩት ቡድኖችም አላይድ ዴሞክራቲክ ኃይሎች (ADF) እና አል-አንሳር አል-ሱና ናቸው፡፡

እኚህ ታጣቂዎች ራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ ከሚጠራው አይ ኤስ አይ ኤስ እና ከአልሻባብ ቡድኖች ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሏል እንደ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገባ፡፡

መሪዎቻቸውም “በልዩ ሁኔታ የተሰየሙ ዓለም አቀፍ አሸባሪዎች” ተብለዋል በቀጣይም በእነዚ መሪዎች ላይ አሜሪካ ማዕቀብ ትጥልባቸዋለች ነው የተባለው፡፡

የሞዛምቢኩ አንሳር አል-ሱና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በደርዘን የሚቆጠሩ የሽብር ጥቃቶች ላይ ተጠያቂ ሲሆን ከጥቅምት 2017 ጀምሮ ከ 1 ሺህ 300 በላይ ዜጎችን ለህልፈት ዳርጓል ሲል ዘገባው አስታውሷል ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *