ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ እንዲለቀቁ ተወስኗል፡፡

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡

በተጨማሪም የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ወይዘሮ ሕርቲ ምህረተአብ እና የክልሉ መንግስት አማካሪ የነበሩት ወልደጊዮርጊስ ደስታ፣ እንዲሁም በእነ አባይ ወልዱ የክስ መዝገብ ላይ ከሚገኙ ተከሳሾች ውስጥ አምደማርያም ተፈራ በ30 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ተወስኗል፡፡

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ቀዳሚ ምርመራ እስከሚሰማ ድረስ በሰርቪስ ማረፊያ እንዲቆዩ ተወስኗል፡፡

በእነ አባይ ወልዱ መዝገብ 9 ሰዎች ቀዳሚ ምርመራ የቀረበባቸዉ ሲሆን፣ ቀዳሚ ምርመራ እስከሚሰማ ድረስ ማረሚያ ይቆዩ በሚል ዐቃቤ ሕግ ያቀረበዉን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ መፍቀዱም ታዉቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መጋቢት 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *