የቀድሞ የሶማሊያ ፕሬዝደንት አረፉ፡፡

የቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት አሊ ማህዲ ሞሃመድ በትላንትናው እለት ነው በጎረቤት ኬንያ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በ82 ዓመታቸው ማረፋቸው የተሰማው፡፡

ፕሬዝዳንት ሲያድ ባሬ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ እ.ኤ.አ. በ 1991 ወደ ስልጣን የመጡ ሲሆን እስከ 2000 ድረስ በስራ ላይ ቆይተዋል ፡፡

ፕሬዝዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ክብር ሰንደቅ ዓላማዎች ለሶስት ቀናት ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡ መወሰናቸውን ቢቢሲ አፍሪቃ ዘግቧል ፡፡

ብሔራዊ የቀብር ኮሚቴም ተሹሟል ነው ያሉት ሚስተር ፋርማጆ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በያይኔአበባ ሻምበል
መጋቢት 02 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.