በናይጄሪያ 20 የሚደርሱ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው ተሰምቷል።

በሀገሪቱ በሰሜናዊ የኒጀር ክልል ያሉ ትምህርት ቤቶች ለሁለት ሳምንታት ዝግ እንዲደረጉ መወሰኗን ተገልጿል።

ናይጄሪያ ይህንን ለማድረግ የተገደደችው በትምህርት ቤቶች አካባቢ የልጃገረዶች እገታ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ነው ተብሏል።

ለናይጄሪያ ከቦኩሃራም አሸባሪ ቡድን በተጨማሪ በየዋሻው መሸሸጊያቸውን ያደረጉ ሽፍቶችም ከባድ ፈተና እንደሆኑባት ነው የሚገለጸው።

ወደ 300 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ታግተው ከተወሰዱ በኋላ ከሰሞኑ በድርድር እንዲመለሱ መደረጉ ይታወቃል።

መንግስትም ቢሆን አሸባሪዎችንም ሆነ የመንደር ሽፍቶችን ሙሉ በሙሉ የመደምሰስ አቅም እንደሚያንሰው ይነገራል።

በዚህም ናይጄሪያ በትላንትናው እለት ሲቪሊያን ዜጎችን የጦር መሳሪያ ለማስታጠቅና እራሳቸውን ከሽፍቶች እንዲከላከሉ ለማድረግ ውሳኔ ማሳለፏ ይታወሳል።

አሁን ደግሞ ትምህርት ቤቶችን ለተወሰኑ ጊዜያት ለመዝጋት ግድ ሆኖባታል ተብሏል።

በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *