አሜሪካ በሀምሌ የነፃነት ቀኗን ከኮቪድ ነፃ ሆና ለማክበር ተስፋ አድርጋለች፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በነፃነት ቀናችን ጁላይ 4 የሀገራቸን ህዝብ በሙሉ ተከትቦ ነፃነት ቀንን ከኮቪድም ነፃ ሆነን እንደምናከብር ተስፋ አለኝ ብለዋል፡፡

ሁሉንም ግዛቶች በፈረንጆቹ ግንቦት 1 ለክትባት ብቁ የሆኑትን ዕድሜያቸው የደረሰ መከተብ የሚችሉ ዜጎችን እንዲከትቡ ትዕዛዝ እንደሚያስተላልፉም ገልፀዋል፡፡

ኮቪድ 19 አለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑ የተገለፀበትን አንደኛ አመት አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት ፕሬዝዳንቱ አሜሪካ ከኮቪድ ነፃ ሆና የነፃነት ቀኗን ታከብራለች ብለዋል፡፡

እስካሁን ግማሽ ሚሊዮን አሜሪካውያን በኮቪድ 19 ሞተዋል፡፡

በንግግራቸው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በነፃነት ቀናችን ሀምሌ 4 አሜሪካውያን ከወዳጆቻችሁ እና ከቤተሰባችሁ ጋር በጓሯችሁ ተሰባስባችሁ የማክበር እድል እንዳላችሁ ላሳውቃቹ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

በስፋት ህዝቡን ለመከተብ እቅድ እንደተያዘ ፕሬዝዳንቱ የተናገሩ ሲሆን ክትባት የሚያከናውን ተንቀሳቃሽ ቡድን በየመንደሩ ይዞራል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሄኖክ አስራት
መጋቢት 03 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *