የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ እድለኛ ታወቋል ብሏል፡፡
የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪ የሆነዉ ክንዴ አስራት በእንቁጣጣሽ ሎተሪ በገዛቻዉ 3 ሎተሪ ትኬቶች የ12 ሚሊዮን ብር አሸናፊ መሆኑን የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ነዋይ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ዕድለኛዉ የሎተሪ ሽልማት የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ 4 ቀን ሲቀረዉ እንደተገኝም ታዉቋል፡፡
እድለኛው ለተፈናቃዮች ከአርባ ምንጭ ያሰባሰበውን የተለያየ አይነት ያላቸው አቃዎች ገቢ ለማድረግ ወደ ከንባታ ዱራሜ በመሄድ ላይ ሳለ በገዛው ሎተሪ ነው አሸናፊ መሆን የቻለው፡፡
ወጣቱ የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ቋሚ ገቢ የሌለው እና የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ነው እንደሚተዳደር ነው የገለጸው፡፡
መልካም ስራ ያሸልማል ይሉት ይሔ ነው ወጣቱ ለደግነት ባደረገው ስራ ነው የሎተሪ አሸናፊ መሆን ያስቻለው፡፡
ብሔራዊ ሎተሪ እድለኛው በመገኝቱም ደስ እንደተሰኝ ተናግሯል፡፡
የእንቁጣጣሽ ሎተሪ የ20 ሚሊዮን አሸናፊ እድለኛ ሳይታወቅ እስካሁን መቆየቱ የሚታወስ ነዉ፡፡
ሄኖክ ወልደገብርኤል
መጋቢት 03 ቀን 2013 ዓ.ም











