በፖሊስ በግፍ ለተገደለው ለጆርጅ ፍሎይድ ቤተሰብ 27 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ሊከፈላቸው ነው፡፡

የሚኒፖሊስ ከተማ ለጆርጅ ፈሎይድ ቤተሰብ 27 ሚሊየን ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተወስኖበታል፡፡

የሚኒ ፖሊስ ከተማ ምክር ቤት በሚኒሶታ ግዛት ታሪክ ትልቁ የተባለውን የቅድመ-ፍርድ ካሣን ለመክፈል በሙሉ ድምፅ አፀደቋል።

የፍሎይድ የቤተሰብ ጠበቃ ለግድያ የተሰጠው ትልቁ ካሣ ለጥቁር ሰው ሕይወት መሆኑ ጠንከር ያለ መልዕክት ያስተላልፋል ሲል ተናግሯል፡፡

ፖሊስ በጥቁሮች ላይ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ የሚወስዳቸው እርምጃዎች መቆም አለባቸው ሲልም መልእክቱን አስተላልፏል፡፡

ሄኖክ ወልደገብርኤል
መጋቢት 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *