አባዱላ ገመዳ የክብር ዶክትሬት ተሰጣቸዉ፡፡

የሐረማያ ዮኒቨርስቲ ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ በዛሬዉ እለት ለሁለት ግለሰቦች የክብር ዶክትሬት ማእረግን ሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርስቲው የክብር ዶክትሬት ማእረግን የሰጠዉ ለአቶ አብድላሂ አሊ ሸሪፍ እና አቶ አባዱላ ገመዳ ነዉ፡፡

አቶ አብድላሂ አሊ ሸሪፍ የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸዉ በቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሲሆን የህይወት ዘመን ተሸላሚ በሚል የክብር ዶክትሬት ማእረግ ተሰጥቷቸዋል፡፡

አቶ አባዱላ ገመዳ ደግሞ በሃገሪቱ በፖለቲካው ፣በግብርና፣በትምህርት እና በጤና እንዲሁም በተለያዩ የልማት ስራዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነዉ የክብር ዶክትሬት ማእረግ የተሰጣቸዉ ተብሏል፡፡

በየዉልሰዉ ገዝሙ
መጋቢት 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *