የሐረማያ ዮኒቨርስቲ ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ በዛሬው እለት 573 የሚሆኑ ተማሪዎችን አስመርቋል።

በዛሬው እለት ከተመረቁት 573 እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 175ቱ ሴቶች ናቸው።

ከእጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 501 በመጀመሪያ ድግሪ ፣73 ቱ ደግሞ በሁለተኛ፣በሶስተኛ እና በስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞች የሰለጠኑ ናቸው።

የህክምና ሳይንስ ኮሌጁ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ያደታ ደሴ በዚሁ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ እንደተናገሩት፣ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከተቋቋመ 25 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ ባለፋት 25 ዓመታትም ከ 1 ሺ 500 በላይ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን አካሂዷል ብለዋል።

ከ 25 ዓመታት በፊት በ ሁለት የትምህርት መርሃ ግብሮች ብቻ የመማር ማስተማሩን ስራ የጀመረው ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ሰዓት በመጀመሪያ ፣በሁለተኛ፣በሶስተኛ እንዲሁም በስፔሻሊቲ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎችን እያሰለጠነ ይገኛል ተብሏል።

የህክምና ሳይንስ ኮሌጁ በአሁኑ ሰዓት የኮሮና ቫይረስ የናሙና ምርመራን በማካሄድ ላይ ሲሆን ከ35 ሺህ በላይ የናሙና ምርመራ ማካሄድንም ዶ/ር ያደታ ተናግረዋል ።

በየዉልሰዉ ገዝሙ
መጋቢት 04 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.