ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 120 ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ህይታቸውን አጥተዋል፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት በሰባት ቀን ውስጥ 90 ያህል ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸዉን ያጡ የነበረ ሲሆን፣ ባሳለፍነው ሳምንት ግን ቁጥሩ በ30 ጨምሯል ተብሏል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት የስርጭት መጠኑ በእጅጉ ጨምሮ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡና በቫይረሱ ህይወታቸውን የሚያጡ ግለሰቦች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ነዉ የተባለዉ፡፡

የቫይረሱ ስርጭት ከዚህ የከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን ሳያስከትል መጀመሪያ ላይ እንደነበረው ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የጥንቃቄ እና የመከላከያ መንገዶችን በአግባቡ መተግበር እንዳለበት የጤና ሚንስቴር አሳስቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሄኖክ ወ/ ገብርኤል
መጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *