አየር ላንድ ከ100 ሺህ በላይ የኦክስፎርድና አስትራዘኔካ ክትባቶችን ቀደም ሲል ማስገባቷን አስታዉቃ ነበር፡፡
አሁን ላይ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሀገሪቱ ክትባት ከመስጠት መዘግየት እንደምትፈልግ ገልፃለች።
በሀገሪቱ ክትባቱን ተደራሽ ለማድረግ የተቋቋመው ኮሚቴም ስራውን እንዲያቆም ተደርጓል ተብሏል።
አየርላንድ ይህን ለመወሰን ያበቃትም ክትባቱ የደም መርጋትን ያመጣል ከተባለ ወዲህ እንደሆነ ነው የተነገረው።
በዚህም ጉዳዩ እውነት መሆን አለመሆኑ ሳይታወቅ ዜጎቼን ከመከተብ ለጊዜው አቁሚያለሁ ብላለች አየርላንድ።
የአለም የጤና ድርጅት በበኩሉ ክትባቱ ከደም መርጋት ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው በተደጋጋሚ ሲገልፅ መቆየቱ ይታወሳል።
ክትባቶችን አምራች ተቋማትም ቢሆኑ ክትባቱ በተከታታይ ሙከራዎች ያለፈ በመሆኑ የደም መርጋትን አያመጣም ማለታቸውን ቢያስታዉቁም ሀገሪቷ ግን ክትባቱን ለመጠቀም ጥርጣሬ እንዳደረባት ገልጻለች።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም











