ወደ ህክምና ማዕከላት ከሚገቡ የኮቪድ 19 ተጠቂዎች ዉስጥ አብዛኞቹ ኦክስጂን ያስፈልጋቸዋል፡፡

የጤና ሚንስቴር እንዳለዉ ወደ ኮቪድ- 19 የህክምና ማዕከል ከሚገቡት 100 ግለሰቦች መካከል 61ዱ በተለያየ መጠን ኦክስጂን እንደሚያስፈልጋቸዉ ገልጿል፡፡

ሚንስቴሩ እንዳለዉ ባሁኑ ሰአት ኦክስጂን የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል፡፡

ወደ ህክምና ማዕከላት ከሚገቡ 100 ግለሰቦች 61 የሚሆኑት በተለያየ መጠን ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፤ 7 ያህል ግለሰቦች ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ ነዉ የተባለዉ።

ይህም ኮቪድ-19 ወደ ኢትዮጵያ ከገባ እለት ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን 2 ሺህ 550 ሰዎች በኮቪድ 19 ምክንያት ለሞት የተዳረጉ ሲሆን 469 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ህክምና ክፍል ዉስጥ እንደሚገኙ ከጤና ሚንስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *