የላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል ለቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር ተሸጠ፡፡

በፍል ውሃ አገልግሎት ድርጅት ስር ሲተዳደር የቆየው የላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል ለቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አክሲዮን ማህበር መሸጡን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

የመንግስት ልማት ድርጅቶች የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ ለኢቲዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ የላንገኖ ሪዞርት ሆቴል የተሸጠዉ ከ54 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ብዙም ባልበለጠ ዋጋ ነዉ፡፡

የሽያጭ ስምምነቱም መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም መከናወኑን አቶ ወንዳፍራሽ ነግረዉናል፡፡

የሽያጭ ዋጋውንም ገዥው ሙሉ በሙሉ ከፊርማው በፊት ገቢ ማድረጉን ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

ሪዞርት ሆቴሉ ወደ ግሉ ዘርፍ እንዲዛወሩ ከተያዙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አንዱ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

በረድኤት ገበየሁ
መጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *