የሸማቾች መብቶች ጥበቃ ማህበር ተመሰረተ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመጀመሪያ ጊዜ አለም አቀፍ የሸማቾች መብቶች ቀንን ዛሬ እያከበረ ይገኛል።

በእለቱም በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስተባባሪነት የሸማቾች መብቶችን ማስጠበቅ የሚያስችል ማህበር ተመስርቷል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዱልፈታህ ዩሱፍ እንደተናገሩት ሸማቾች በንግድ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ሊኖራቸው የሚችለውን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሲባል ማህበሩን ለማቋቋም ብዙ ስራዎች ከተሰሩ በኋላ አሁን ምስረታውን እውን ለማድረግ በቅተናል ብለዋል።

አቶ አብዱልፈታህ ማህበሩ ዜጎች በኢኮኖሚው ዘርፍ ፍትሃዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚሰራ መሆኑን ገልፀው የንግድ ስርአቱን ለማዘመንም ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ነዉ ያሉት፡፡

ማህበሩ በዋናነት ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመከታተል ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችሉ ስራዎችን ይሰራልም ብለዋል።

በዚህም የሸማቾችን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ጥራታቸው የተጓደሉ ምርቶችን ለሸመታ የሚያቀርቡ ነጋዴዎችን ህጋዊ አሰራራቸውን ይከታተላል ነው ያሉት ሃላፊው።

በምርቶቹ ባዕድ ነገሮችን በሚቀላለቅሉ፣ ሚዛን በሚያጎድሉ፣ ያለፈቃድ በሚሰሩ፣ የተከለከሉ ነገሮችን በሚነግዱና ሌሎችንም አግባብ ያልሆኑ ንግዶችን የሚነግዱ ነጋዴዎችን ለህግ ያቀርባል ሲሉ ገልጸዋል።

በመሆኑም ሸማቾች ገንዘባቸውን አውጥተው የፈለጉትን ምርት በህጋዊ ዋጋ ገዝተው በሸመቱት ምርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመስራት ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ገበያውን ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማድረግ እንደሚሰራም ገልጸዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *