የታክሲ ስምሪት ላይ የተፈጠረዉ ችግር ምንድን ነዉ?

በዛሬዉ እለት በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በፒያሳ፣አዲሱ ገብያ፣በአጎናና በሌሎችም አካባቢዎች ከፍተኛ የታክሲ ትራንስፖርት ችግር ተስተዉሏል፡፡

በዚህም ረጃጅም የታክሲ አገልግሎት ፈላጊ ሰልፎችን ተመልክተናል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳረጋገጠዉ አሽከርካሪዎቹ ሪከርድ ይቅርልን፣የትራንስፖርት ስምሪት አሰጣጡ ፍትሃዊ አይደለም፣ ስምሪት ተቆጣጣሪዎችም በአግባቡ እያስተናገዱን አይደለም የሚሉ ቅሬታዎች አሏቸዉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ ኢንጅነር ስጦታዉ አካለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣አገልግሎትን በማቆምና ህዝብን በማጉላላት ጥያቄን ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፤ጥያቄም ቢኖር እንኳ አገልግሎት ሳይቋረጥ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

የታክሲ አሽከርካሪዎችን ጥያቄ ለማድመጥና በመፍትሄዉ ላይ ለመምከር እየሞከርን ነዉ ያሉት የቢሮ ሃላፊዉ፣ ትክክለኛ ጥያቄ ያላቸዉ እንዳሉ ሁሉ ሌላ አላማ አንግበዉ ህዝብ እንዲጉላላ የሚያስተባበሩ አካላትንም ተመልክተናል ነዉ ያሉት፡፡

እነዚህንም ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመተባበር እንዲያዙና በህግ እንዲጠየቁ እያደረግን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በአባቱ መረቀ
መጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.