46 አሽከርካሪዎች እና 10 ረዳቶች በጸጥታ አስከባሪዎች ተይዘዉ ይገኛሉ፡፡

አሽከርካሪዎችና ረዳቶች በጸጥታ አስከባሪዎች የተያዙት በዛሬው እለት የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ያልተገባ መልእክት አስተላልፈዋል በሚል ነዉ፡፡

በአዲስ አበባ በዛሬው እለት የትራንስፖርት እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ማጋጠሙም ከዚሁ ከስራ ማቆም ጋር የተገናኝ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

አሽከርካሪዎቹ ያለፍቃድ በከተማዋ ያልተገባ መልእክት እና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበርም ተገልጿል፡፡

የስራ ማቆም አድማ ካደረጉ አሽከርካሪዎች መካከል 56 ያህሉ ለጊዜው ተይዘው ጉዳያቸው እየታየ እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሚኒኬሽን ሀላፊ ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ኮማንደሩ አክለዉም አሽከርካሪዎች እና ረዳቶች እስር ላይ አይገኙም ጉዳቸው ተጣርቶ እስከ ማታ ድረስ ይለቀቃሉ ብለዋል፡፡

በከተማዋ የተፈጠረውን የትራንስፖርት እጥረት ለመቅረፍ ከትራንስፖርት ባለስልጣን ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝም ኮማንደር ፋሲካው ነግረዉናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 06 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *