ለ10 ዓመታት የቀጠለዉ የሶሪያ ግጭት!

በሶሪያ ደም አፋሳሽ ግጭት ከተቀሰቀሰ 10 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

እ.ኤ.አ 2011 የተቀሰቀሰው ግጭት ያለምንም መረጋጋት ለተከታታይ አስርት አመታት ዘልቋል፡፡

በወቅቱ የፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ አስተዳደር ያልተመቻቸው ሶሪያውያን ዜጎች፣ በሰላም ስልጣናቸውን ማስለቀቅ አልሆን ሲላቸው፣ፕሬዝዳንቱን በሃይል ለማስለቀቅ ነበር ወደ አመጽ የገቡት፡፡

አመፁ ቀስበቀስ ሌሎች የውስጥ አሸባሪ ቡድኖችን በማካተት በሀገሪቱ የገዥው መንግስትና አማፅያን መካከል የለየለት የእርስ በርስ ጦርነት ሆኖ አረፈዉ፡፡

በተለይ የሶሪያን ጦርነት አሁንም ድረስ እንዳይበርድ ያደረገው በውጭ ሃይሎች የሚደገፍ በመሆኑ እንደሆነ ይነገራል፡፡

የገዥውን የአላሳድ መንግስት በጦር መሳሪያና በወታደራዊ ሃይል በዋናነት በሩሲያና ኢራን ድጋፍ ያገኛል፡፡

ተቃዋሚ ሃይሎችም ቢሆኑ በሌሎች ሀገራት ያልተቆጠበ ድጋፍ አላቸዉ፡፡

በዚህም ሶሪያዊያን ለአስርት አመታት በእርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ ይገኛሉ፡፡
በዚህ የእርስ በርስ ጦርነት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡

ከ20 ሚሊዮን በላይ ሶርያውያን ዜጎች ደግሞ ቀያቸዉን ለቀዉ ወደ ሌሎች አካባቢዎችና ሃገራት ተሰደዋል፡፡

ሮይተርስ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በጅብሪል ሙሃመድ
መጋቢት 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *