በዛሬዉ እለት 150 ኢትዮጵያዊያን ከየመን ወደ ሀገራቸዉ ይመለሳሉ ተባለ፡፡

በየመን በደረሰው የእሳት አደጋ የ 43 ዜጎች ቀብር መፈፀሙንና 150 የሚሆኑት ደግሞ በዛሬው ዕለት አገር ውስጥ ይገባሉ ተብሏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ ከሳምንት በፊት በየመን በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ምክንያት 43 ዜጎች መሞታቸውንና ከነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሳይሆኑ እንዳልቀረና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ተቀብረዋል ብሏል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ሲሆኑ ፣በየመን የሞቱትን ማንነት መንግስት እያጣራ ይገኛል ነው ያሉት።

በየመን ባለው ቀውስ ምክንያት ችግሩን በግልፅ ለማወቅ አስቸጋሪ እንደሆነ ያስታወቁት አምባሳደሩ ፣ በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዛሬው ዕለትም 150 ኢትዮጵያውያን ከየመን ኤደን ከተማ ወደ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሏል።

በየመን ጦርነት ምክንያት በሰናኣ ያለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በመዘጋቱ ኦማን ያለው ቆንስላ ፅህፈት ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ እንደሚገኝም ቃል አቀባዩ አንስተዋል ።

በቀጣይም በየመን የሚገኙ ስደተኞችን ወደ አገር ውስጥ ለመመለስ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እየቸሰራ ነው ተብሏል ።

በአባቱ መረቀ
መጋቢት 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *