አየርላንድ በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷ እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ አስታውቀች፡፡

የአየርላድ መንግስት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክርቤት እያደረገች ያለው ጣልቃ ገብነት በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት እንደሌለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሁለቱ አገራት ካላቸው ታሪካዊ ግንኙነት አኳያ፣ አሁን እየሄደችበት ያለው መንገድ ትክክል አለመሆኑን ገልጸዋል።

በአየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት እሸቱ ደሴ መንግስት እንደጠራቸው የገለፁት ቃልአቀባዩ ይህ ማለት ግን በአየርላንድ ያለውን ኢምባሲ ለመዝጋት ሳይሆን ለውይይት እንደሆነ አንስተዋል።

አምባሳደር እሸቱ ደሴ ከመንግስት ጋር ስለ በአየርላንድ ወቅታዊ ሁኔታ ይወያያሉ ተብሏል።

የአየርላንድ መንግስት የኢትዮጵያን ልማት ለመደገፍ የተለያዩ ስራዎችን ስትሰራ እንደነበረ ያስታወሱት አምባሳደር ዲና አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያን በተሳሳተ መንገድ መመልከቷ ተገቢ አይደለም ብለዋል።

ኢትዮጵያ በአየርላንድ ያላትን ኢምባሲ ልትዘጋ ነው የሚለው ግን የተሳሳተ እንደሆነም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

በአባቱ መረቀ
መጋቢት 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *