የማሊ ፍርድ ቤት የአማዱ ሶኖጎን የፍርድ ሂደት አቋረጠ፡፡

አማዱ ሶኖጎ በማሊ በፈረንጆቹ 2012 የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት መርተዋል በሚል ለእስር ተዳርገዉ የፍርድ ሂደታቸውን ሲከታተሉ ነበር፡፡

አማዱ ሶኖጎ ለ21 ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ ምክንያት ናቸዉ በሚልም ስማቸዉ ይነሳል፡፡

ከዚሁ የመፈንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘም የሀገሪቱ መንግስት እና ለእስር ተዳርገው የነበሩ ዜጎች በ2019 እርቀ ሰላም ያወረዱ ቢሆንም አማዱ ሶኖጎ በእስር እንዲቆዩ ተደርጎ ነበር፡፡

አሁን ላይ ፍርድ ቤቱ በነጻ እንዲሰናበቱ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ የ15 ተከሳሾች የክስ ሂደት ማቋረጡንም አስታውቋል፡፡
አልጀዚራ

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 07 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.