ፓርኩ በሃገሪቱ በነበረው የፀጥታ ችግር ሳቢያ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ መግባት አልቻልኩም ብሏል፡፡
በሃገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት በተፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች የውጪ ባለሃብቶች ወደ ፓርኩ ገብተው ኢንቨስት ለማድረግ እንዳልቻሉ የፓርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ካሚል ኢብራሂም ለ ኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
በፓርኩ ከሚገኙ 15 ማምራቻ ሼዶችም እስካሁን ወደ ስራ የገቡት አራቱ ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በፓርኩ በመጀመሪያ ዙር ግንባታቸው የተጠናቀቁ 15 የማምራቻ ሼዶች ለስራ ዝግጁ ቢሆኑም፣ በሃገሪቱ የሚከሰቱ ግጭቶች ባለሃብቶችን ለኢንቨስትመንት ለመሳብ ትልቅ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን ነው የፓርኩ ዋና ዳሬክተር አቶ ካሚል ኢብራሂም የተናገሩት፡፡
የድሬዳዋ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ከ 3 ሺ ስኬዌር ሜትር እስከ 11 ሺ ስኬዌር ሜትር ስፋት ያላቸው 15 የማምረቻ ሼዶች ያሉት ሲሆን ፓርኩ ዘመናዊ የመኖሪያ ቪላዎችን ጨምሮ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ያሟላ ነው፡፡
እ ኤ አ በ 2020 ተጠናቆ ወደ ስራ የገባው ፓርኩ ግንባታው 150 ሚለዮን ዶላር የሚሆን ወጪ ወቶበታል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በየዉልሰዉ ገዝሙ
መጋቢት 07 ቀን 2013 ዓ.ም











