የመጀመርያዉ አደጋ የደረሰው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት በንግድ ሱቆች ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡
በዚህ አደጋ ምክንያትም 2 ሚሊየን 125 ሺህ የሚጠጋ ንብረት ጉዳት የደረሰበት ሲሆን ወደ 12 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ማዳን እንደተቻለ ነው የተገለጸው፡፡
ከዚሁ አደጋ ጋር በተያያዘም አንድ ሰው የመቁሰል አደጋ ደርሶበታል ተብሏል፡፡
ሌላኛው አደጋ የደረሰው በኮልፌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ሆላንድ ኤምባሲ አካባቢ በእንጨት ክምር ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ነው፡፡
በአደጋው ሳብያ 50 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ለውድመት ሲዳረግ ወደ 60 ሚሊየን የሚጠጋ ንብረት ደግሞ ከውድመት ማዳን ተችሏል ተብሏል፡፡
በሁለቱም ድንገተኛ አደጋዎች የሰው ህይወት እንዳልጠፋ የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በሄኖክ ወ/ገብርኤል
መጋቢት 08 ቀን 2013 ዓ.ም











