ተቋማት የግዢ እቅድ ባለመጠቀማቸው የንብረት ክምችት እያጋጠመ ነው ተባለ፡፡

ንብረት እያላቸው ተመሳሳይ የሆነ ተጨማሪ መገልገያ ንብረት ግዢ የሚፈጽሙ ተቋማት ባልተገባ መልኩ ንብረት እያከማቹ እንደሆነ ነው የተገለጸዉ፡፡

የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰጠኝ ገላን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት አንዳንድ ተቋማት የማያሰፈልጋቸውን ንብረት ሌላ ቦታ እጥረት እያለ አከማችተው የሚይዙ አሉ ብለዉናል፡፡

ለዚህ ዋነኛው ምክንያት ተቋማት በአመት ምን ያህል መገልገያ ንብረት ያስፈልገናል ብለው የግዢ እቅድ ስለማይጠቀሙ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት 15 ተቋማት ላይ ድንገተኛ ዳሰሳ ተደርጎ ያላግባብ ተከማችተው የተገኙ ንብረቶች በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ የተደረገባቸው መሆናቸውን ታዝበናል ነዉ ያሉት፡፡

በፌደራል መንግስት በጀት የሚለቀቅላቸው ተቋማት ላይ ጥናት ተደርጎ ምን ያህል ኪሳራ ሀገሪቱ እንደደረሰባት በግልጽ ባይታወቅም ከፍተኛ የንብረት ክምችት መኖሩ ግን ተረጋግጧል ብለዉናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን https://t.me/ethiofm107dot8 ይቀላቀሉ።
በመቅደላዊት ደረጀ
መጋቢት 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.