ትራምፕ ደጋፊዎቻቸዉ የኮቪድ 19 ክትባት እንዲወስዱ አሳሰቡ፡፡

በአሜሪካ የኮቪድ 19 ክትባትን ከሚቃወሙ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ዋነኞቹ የትራምፕ ደጋፊዎች መሆናቸዉ ይነገራል፡፡

ይህን ተከትሎም የአሜሪካ ብሔራዊ የአለርጂ እና ተላላፊ በሽታዎች ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አንቶኒ ፋዉቺ ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸዉ ምክር እንዲያስተላለፉ ጠይቀዉ ነበር፡፡

የትራምፕ ደጋፊዎች በክትባቱ ላይ ተቃዉሟቸዉን የሚገልጹት በሌሎች ሀገራት እንደሚታየዉ ክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት አለዉ በሚል ሳይሆን ለትራምፕ ያላቸዉን ድጋፍ ለመግለጽ ነዉ ተብሏል፡፡

የቀድሞዉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የቫይረሱን አደገኛነት አሳንሰዉ ሲገልጹ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸዉ ባስተላለፉት መልዕክትም “ክትባቱን ዉሰዱ በዚህም ተጠቃሚ ትሆናለችሁ” ብለዋቸዋል፡፡

በሲ ቢ ኤስ ኒዉስ በተሰራ የዳሰሳ ጥናት አብዛኞቹ የሪፐብሊካን ደጋፊዎች ክትባት የማግኘት እድሉ ተመቻችቶላቸዉ የመከተብ ፍላጎት እንዳላሳዩ ገልጿል፡፡
ቢቢሲ

በሙሉቀን አሰፋ
መጋቢት 08 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *